ኢትዮጵያና ህንድ በድንበር ተሻጋሪ የጤና ክብካቤ ትብብር ለማጠናከር እንደሚፈልጉ ገለፁ
15:11 12.10.2025 (የተሻሻለ: 15:24 12.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያና ህንድ በድንበር ተሻጋሪ የጤና ክብካቤ ትብብር ለማጠናከር እንደሚፈልጉ ገለፁ
በኢትዮጵያ የህንድ ኤምባሲ “በእሴታዊ የህክምና ጉዞ የግንኙነት ድልድይ መፍጠር" በሚል መሪ ቃል የጤና ክብካቤ ጉባኤ አዘጋጅቷል።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሑሪያ አሊ ህንድ የላቀ ህክምና ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ተመራጭ እንደሆነች በዚህ ወቅት ተናግረዋል።
ህንድ በህክምናው ዘርፍ ያካበተችውን እውቀት ከኢትዮጵያ ራዕይ ጋር በማጣመር ጠንካራ፣ ተደራሽ እና ሕዝብ ተኮር የጤና ክብካቤ ሥርዓቶችን መፍጠር ይቻላልም ብለዋል።
የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ በበኩላቸው በህንድ አቅራቢዎችና በኢትዮጵያ ባለድርሻ አካላት መካከል ትብብር ለማስፋት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ገልፀዋል።
ህንድ በኢትዮጵያ የመድኃኒት ማምረት አቅምን በማጠናከር ተመጣጣኝ እና ጥራት ያለው ህክምና ለማረጋገጥ እየተባበረች እንደሆነም አስታውቀዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
