የማዳጋስካር ቀውስ፦ እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየማዳጋስካር ቀውስ፦ እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች
የማዳጋስካር ቀውስ፦ እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.10.2025
ሰብስክራይብ

የማዳጋስካር ቀውስ፦ እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች

▪ፖሊሶች ዛሬ ከተቃዋሚ ሰልፈኞች ጎን መቆማቸው ተዘግቧል። የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን እንደዘገበው ፖሊሶች “እኛ እዚህ ያለነው ለመጠበቅ እንጂ ለማሸበር አይደለም” የሚል መግለጫ አውጥተው የጦር ሠራዊቱ ኃይል እንዳይጠቀም አሳስበዋል።

▪አንድ የጦር ሠራዊቱ ክንፍ ትናንት ሰልፈኞቹን መቀላቀሉ ተሰምቷል። በማዳጋስካር ዋና ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የአስተዳደር እና ቴክኒካል ሠራተኞችና አገልግሎት የጦር ኃይል አባላት (ካፕሳት)፤ ወታደሮች “በተቃዋሚዎች ላይ ተኩስ የመክፈት ትዕዛዝ እንዳይቀበሉ” ጥሪ አቅርበዋል።

▪የማዳጋስካር ጦር ኃይል ባለፈው እሁድ ባወጣው መግለጫ፤ የመሬት፣ የአየር እና የባሕር ኃይሎችን ያካተተው የጦር ኃይሎች አመራር ቅንጅት ከአሁን በኋላ የሚመራው በካፕሳት የትዕዛዝ ማዕከል መሆኑን አስታውቋል።

▪በዚያው ምሽት የካፕሳት ወታደሮች ወደ ዋና ከተማው በመግባት ከፕሬዝዳንቱ ታማኝ የደህንነት ኃይሎች ጋር ለአጭር ጊዜ የተኩስ ልውውጥ ካደረጉ በኋላ መሀል አንታናናሪቮን በመቆጣጠር ሰልፈኞቹን ተቀላቅለዋል።

▪ፕሬዝዳንቱ ድርጊቱን “ሥልጣንን በኃይል ለመንጠቅ የተደረገ ሕገ-ወጥ ሙከራ” ሲሉ አውግዘው፤ ሁሉም ብሔራዊ ባለድርሻ አካላት “ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓትን እና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን ለመከላከል” እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል።

▪የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ኤር ኦስትራልን እና ኤር ፍራንስን ጨምሮ በርካታ አየር መንገዶች ከቅዳሜ እስከ ሰኞ ወደ ማዳጋስካር የሚደረጉ በረራዎች ወደፊት መተላለፋቸውን ወይም መሰረዛቸውን አስታውቀዋል።

▪አንታናናሪቮ ተቃውሞዎች ከተጀመሩበት ከመስከረም ወር አጋማሽ ወዲህ ትልቁን ሰልፍ አስተናግዳለች። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ግንቦት 13 ተብሎ በሚጠራው አደባባይ እንደተሰበሰቡ ተዘግቧል። የእንቅስቃሴው ዋና አካል ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊናን እና የሴኔት ፕሬዝዳንቱ ሥልጣን እንዲለቁ የሚጠይቀው የ "ጀን ዚ" ስብስብ ነው።

▪በርካታ መገናኛ ብዙኃን አንድሪ ራጆሊና ሀገሪቱን ለቀው እንደወጡ ቢዘግቡም፤ የፕሬዝዳንቱ ፅሕፈት ቤት “ፕሬዝዳንቱ አሁንም በሀገሪቱ ክልል ውስጥ ይገኛሉ” ሲል ትናንት አስተባብሏል።

ከማኅበራዊ የትስስር ገፆች የተገኙ ምሥሎች

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የማዳጋስካር ቀውስ፦ እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የማዳጋስካር ቀውስ፦ እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የማዳጋስካር ቀውስ፦ እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0