የመፅሀፍ ቅዱስ የኤደን ገነት ባህር ዳር ናት የሚል ዓለም አቀፍ ጥናት ይፋ ተደረገ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየመፅሀፍ ቅዱስ የኤደን ገነት ባህር ዳር ናት የሚል ዓለም አቀፍ ጥናት ይፋ ተደረገ
የመፅሀፍ ቅዱስ የኤደን ገነት ባህር ዳር ናት የሚል ዓለም አቀፍ ጥናት ይፋ ተደረገ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.10.2025
ሰብስክራይብ

የመፅሀፍ ቅዱስ የኤደን ገነት ባህር ዳር ናት የሚል ዓለም አቀፍ ጥናት ይፋ ተደረገ

አሜሪካዊው ምሁር መሐሙድ ጀዋይድ መጽሐፍ ቅዱስን እና ቅዱስ ቁርዓንን ጨምሮ በርካታ መዛግብትን በማመሳከር ያካሄዱት ሳይንሳዊ ጥናት ትክክለኛው የገነት መገኛ ባህር ዳር መሆኗን አረጋግጧል ብለዋል፡፡

ይህም በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱት ግዮን፣ ኤፍራጥስ፣ ጤግሮስና ፒሶን ታላላቅ ወንዞች በዘመናዊቷ ኢራቅ ውስጥ ስለሚጓዙ ኤደን በዚያ አካባቢ መሆን አለበት ከሚለው እምነት ጋር የተቃረነ ነው፡፡

በአቻ-ያልተገመገመው ጥናት የብሉ ናይል ወንዝ የመጽሐፍ ቅዱሱ ግዮን አቻ ሊሆን እንደሚችል እና የጣና ሀይቅ ፈሳሾች ወደ ብዙ የውሃ መስመሮች ተከፍለው በዘፍጥረት የተገለጹትን አራቱን ወንዞች ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ጠቁሟል።

"ሁሉም ፍንጮች ወደ ባሕር ዳር፣ ወደ ጣና ሐይቅ አቅራቢያ ይጠቁማሉ፡፡ አስደናቂ ውበት፣ አያሌ ዕፅዋት እና የብሉ ናይል ምንጭ፤ ይህም ከጥንቱ የኤደን ወንዞች ገለጻ ጋር የሚገጥም ነው” በማለት መሐሙድ ጀዋይድ ፅፈዋል።

ጃዋይድ በመጽሐፍ ቅዱስ እና ቅዱስ ቁርዓን የሰፈሩት የአዳም (አደም) እና ሄዋን (ሀዋ) ዘፍጥረት በመተንተን አዳም (አደም) የተፈጠረበት ትክክለኛ ቦታ ከዓባይ (ግዮን) ወንዝ እና የጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ አካባቢ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን አቅርበዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0