ካሜሮናውያን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ወደ ምርጫ ጣቢያ እየተመሙ ነው
12:35 12.10.2025 (የተሻሻለ: 12:44 12.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ካሜሮናውያን ፕሬዝዳንታቸውን ለመምረጥ ወደ ምርጫ ጣቢያ እየተመሙ ነው
🟠 ከ8 ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምጻቸውን ለመስጠት ብቁ ናቸው፡፡
🟠 በዛሬው ዕለት ለሚካሄደው የአንድ ዙር ምርጫ በጠቅላላው 31 ሺህ 653 የምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተዋል።
🟠 ተመራጩ ፕሬዝዳንት ለሰባት ዓመት የሥልጣን ዘመን ያገለግላሉ።
🟠 ለ43 ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆዩት የአሁኑ ፕሬዝዳንት ፖል ቢያ፤ ለምርጫ ከቀረቡት 12 እጩዎች መካከል አንዱ ናቸው።
🟠 ፕሬዝዳንቱ ከዋናዎቹ የተቃዋሚ እጩዎች ኢሳ ቺሮማ ባካሪ እና ቤሎ ቡባ ማይጋሪ ጋር ይፎካከራሉ።
🟠 ሕገ-መንግሥታዊ ምክር-ቤት የምርጫውን የመጨረሻ ውጤት እስከ ጥቅምት 16 ድረስ የማወጅ ግዴታ አለበት።
የሀገሪቱ ምርጫ የበላይ አካል 'ኤሌካም'፤ ሕገ-መንግሥታዊ መመዘኛዎችን የሚያሟላ፣ ግልጽና ሁሉን አቀፍ የምርጫ ሂደት ለማረጋገጥ ሁሉም አስፈላጊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን አጽንዖት ሰጥቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X