የእስራኤል ጦር በጋዛ ቀሪ የሃማስ ዋሻዎችን ያወድማል - የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየእስራኤል ጦር በጋዛ ቀሪ የሃማስ ዋሻዎችን ያወድማል - የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር
የእስራኤል ጦር በጋዛ ቀሪ የሃማስ ዋሻዎችን ያወድማል - የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 12.10.2025
ሰብስክራይብ

የእስራኤል ጦር በጋዛ ቀሪ የሃማስ ዋሻዎችን ያወድማል - የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር

ይህ ተግባር የሚከናወነው ታጋቾች ከተለቀቁ በኋላ በዓለም አቀፍ ኃይሎች እገዛ ይሆናል ሲሉ እስራኤል ካትዝ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ፤ "ይህ በስምምነቱ የጋዛን ወታደራዊ ኃይል ማስወገድ እና ሃማስን ትጥቅ ማስፈታት መርህ ዋና ነጥብ ነው" ብለዋል።

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ለዚህ ተልዕኮ ዝግጅት እንዲያደርግ መመሪያ ሰጥተዋል።

ሃማስ ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ከደረሰ ሰዓታት በኋላ የጋዛ ሰርጥን እንደገና መቆጣጠር ጀምሯል ሲል የምዕራባውያን ጋዜጣ የአካባቢውን ነዋሪዎች ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

በጋዜጣው ቃለመጠይቅ የተደረገላቸው የጋዛ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ ታጣቂ ቡድኑ ቁጥጥሩን መልሶ ለማጠናከር እና ሂሳብ ለማወራረድ በጋዛ በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ይገኛል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0