በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በማዕከላዊ ለንደን በመሰባሰብ ፍልስጤምን የሚደግፍ ሰልፍ አካሄዱ
20:25 11.10.2025 (የተሻሻለ: 20:34 11.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በማዕከላዊ ለንደን በመሰባሰብ ፍልስጤምን የሚደግፍ ሰልፍ አካሄዱ
የተቃውሞ ሰልፉ የፍልስጤም የአብሮነት ዘመቻ የተባለው ቡድን እና እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን እርምጃ እንዲሁም እንግሊዝ ለእስራኤል የምታቀርበዉን የጦር መሣሪያ ሽያጭ የሚቃወሙ ሌሎች ቡድኖች፣ "ጦርነቱ ይቁም" ከተባለው ቡድን ጋር በአንድነት የተዘጋጀ ነው ሲል የስፑትኒክ ዘጋቢ ዘግቧል።
ተሳታፊዎች የፍልስጤም ሰንደቅ ዓላማ ያነገቡ ሲሆን፣ "በጋዛ የሚካሄደውን የዘር ማጥፋት አቁሙ" ፣ "ጋዛን አታስርቡ" እና "ለእስራኤል የጦር መሣሪያ አቅርቦትን አቁሙ" የሚሉ መፈክሮች የተጻፉባቸውን ምልክቶች ይዘው ነበር።
ሌሎች ደግሞ "ያለ ፍትሕ ሰላም የለም" እና "ይሁን ለአይሁድ እምነት፣ አይሁን ለጽዮናዊነት" የሚሉ መፈክሮችን ያሰሙ ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X