60 የሚሆኑ የሐማስ ታሳሪዎች ብቻ ይለቀቃሉ፡ የመጨረሻው ዝርዝር ይፋ ሆነ
19:35 11.10.2025 (የተሻሻለ: 19:44 11.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
60 የሚሆኑ የሐማስ ታሳሪዎች ብቻ ይለቀቃሉ፡ የመጨረሻው ዝርዝር ይፋ ሆነ
195 የሐማስ ታሳሪዎችን የመፍታት ሂደት ተጠናቅቋል፤ ነገር ግን 60 ያህሉ ብቻ እንደሚለቀቁ እርግጥ መሆኑን የእስራኤል ሚዲያ ዘግቧል።
የእስራኤል የደህንነት አገልግሎት (ሺን ቤት) ወደ 100 የሚጠጉ ሥሞችን ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ 25 ታዋቂ መሪዎችንም ከዝርዝሩ ውስጥ አስቀርቷል።
እንዲፈቱ ሥማቸው የተዘጋጀው ፍልስጤማውያን እስረኞች የዕድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸውን ብቻ ያካትታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ዕቅድ ለሚቀጥለው ምዕራፍ ስምምነት ላይ መደረሱን ያስታወቁ ሲሆን፣ ታጋቾች ሰኞ እንደሚመለሱ አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X