ቱርክ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ሰርጥ ለማሰማራት እያጤነች መሆኑን የአገሪቱ ገዥ ፓርቲ አስታወቀ
17:47 11.10.2025 (የተሻሻለ: 19:14 11.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቱርክ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ሰርጥ ለማሰማራት እያጤነች መሆኑን የአገሪቱ ገዥ ፓርቲ አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቱርክ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ ሰርጥ ለማሰማራት እያጤነች መሆኑን የአገሪቱ ገዥ ፓርቲ አስታወቀ
የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የመከላከያ ሚኒስቴር እና የደህንነት ኤጀንሲዎች በአሁኑ ጊዜ ዝርዝር ጉዳዮችን እየመረመሩ ነው፤ ሲሉ የቱርክ ፍትሕና ልማት ፓርቲ የፓርላማ ቡድን መሪ አብዱላህ ጉለር ተናግረዋል።
"ይህ የስምምነት ማዕቀፍ አካባቢውን፣ ሁኔታውንና ጊዜውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ይወሰናል ... ከዚያም በኋላ የውሳኔ ሐሳብ ቀርቦ ግምገማ ይካሄዳል" ሲሉ ለቱርክ የመንግሥት የብሮድካስት አገልግሎት ተናግረዋል።
ዝርዝር ጉዳዮች ከተጠናቀቁ በኋላ የቱርክ ወታደሮችን ወደ ጋዛ የመላክ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ ፓርላማው እንዲያፀድቀው ሊቀርብ እንደሚችል አክለዋል።
ጉለር "ጊዜው በጣም ገና ነው፣ እኛ በጉዳዩ ዙሪያ ገና ጅምሩ ላይ ነን" ብለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሐሙስ ዕለት ቴል አቪቭ እና ሐማስ የመጀመሪያው ምዕራፍ የሰላም ዕቅድ ላይ መስማማታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በዚህም መሠረት የእስራኤል ታጋቾች ይለቀቃሉ፤ የፍልስጤም እስረኞችም ይፈታሉ፤ የእስራኤል ወታደሮችም ከጋዛ ይወጣሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X