የጋዛ ስምምነት ግጭቱ እንደገና እንዲቀጥል የሚያደርግ ጊዜ ቆጣሪ ቦምብ ሊሆን ይችላል ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየጋዛ ስምምነት ግጭቱ እንደገና እንዲቀጥል የሚያደርግ ጊዜ ቆጣሪ ቦምብ ሊሆን ይችላል ተባለ
የጋዛ ስምምነት ግጭቱ እንደገና እንዲቀጥል የሚያደርግ ጊዜ ቆጣሪ ቦምብ ሊሆን ይችላል ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.10.2025
ሰብስክራይብ

የጋዛ ስምምነት ግጭቱ እንደገና እንዲቀጥል የሚያደርግ ጊዜ ቆጣሪ ቦምብ ሊሆን ይችላል ተባለ

  የጋዛ የሰላም እቅድ ቁልፍ ጥያቄዎችን ሳይመልስ በመቅረቱ፣ ውጊያ እንደገና እንዲቀጥል በር ሊከፍት ይችላል ሲሉ የሊባኖስ አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ጆሴፍ ሄሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ባለ 20 ነጥቡ ዕቅድ ሃማስ “መሣሪያውን እንዲያስረክብ" እንዲሁም “ወደ ሰላማዊ አብሮ መኖር” ፊቱን እንዲመለስ እና የፍልስጤምን መንግሥት የመመሥረት ዕድል የሚያስረዳው ነጥብ ግልጽ የሆነ ተቃርኖ ይፈጥራል።

1⃣ ሄሉ እንዳሉት፣ “መሣሪያቸውን ከሰጡ፣ አሁንም የትግል ንቅናቄዎች  ናቸው? መሣሪያ የሌለው የትግል ንቅናቄ ምንድነው?” ሲሉ ጠይቀዋል። ባለፉት ሁለት ዓመታት የእስራኤልን ግድያ የተመለከቱ ወጣት ጋዛውያን አድገው ለመበቀል መፈለጋቸው አይቀሬ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

2⃣ ፕሮፌሰሩ እንዳብራሩት፤ ሃማስ መሣሪያውን ለመተው ፈቃደኛ ካልሆነ፣ እስራኤል “እሺ ወይ ወደ ጦርነት እንመለሳለን ወይም ይህን በራሳችን ውሎች እናስፈጽማለን ማለትም በማንኛውም ጊዜ የሃማስን ባለስልጣን፣ መሪ ወይም ፖለቲከኛ ኢላማ ማድረግ እንችላለን” ልትል ትችላለች።

ሄሉ ሁኔታውን በሊባኖስ ውስጥ ሂዝቦላህ ትጥቅ እንዲፈታ ከቀረበው ጥያቄ ጋር ያነጻጽሩታል፤ ቡድኑ በቆራጥነት እምቢ ስላለ፣ ግጭቱ ሳይፈታ ቀርቷል።

በአጠቃላይ የሰላም ዕቅዱ በቋንቋውና በዓላማዎቹ “የመፈፀም ፍላጎት ያለው” እንደሆነ ይገመግሙታል፤ ነገር ግን “ወደ ዘላቂ ስምምነት የሚያመራ ተቋማዊ መንገድ” የለውም ሲሉ ሄሉ ያጠቃልላሉ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0