'የወንጀለል እና ፋሺስታዊ ቅስቀሳ ነው:' ሲሉ የስፔን ፖለቲካኛው የማቻዶ የኖቤል ሽልማት ለሰላም የሚሰጥ ስድብ ነው አሉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ'የወንጀለል እና ፋሺስታዊ ቅስቀሳ ነው:' ሲሉ የስፔን ፖለቲካኛው የማቻዶ የኖቤል ሽልማት ለሰላም የሚሰጥ ስድብ ነው አሉ
'የወንጀለል እና ፋሺስታዊ ቅስቀሳ ነው:' ሲሉ የስፔን ፖለቲካኛው የማቻዶ የኖቤል ሽልማት ለሰላም የሚሰጥ ስድብ ነው አሉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 11.10.2025
ሰብስክራይብ

'የወንጀለል እና ፋሺስታዊ ቅስቀሳ ነው:' ሲሉ የስፔን ፖለቲካኛው የማቻዶ የኖቤል ሽልማት ለሰላም የሚሰጥ ስድብ ነው አሉ

የቬንዙዌላ ተቃዋሚ መሪ ማሪያ ኮሪና ማቻዶ የኖቤል የሰላም ሽልማት መሰጠቱ፣ “የተከበረ፣ የታመነና ጀግና የሆነውን የቬንዙዌላን ሕዝብ” ላይ ያነጣጠረ “የወንጀልና ፋሺስታዊ ቅስቀሳ” ነው፤ ሲሉ የአንዳሉሲያ ፓርላማ ምክትልና የስፔን ኮሚኒስት ፓርቲ አባል የሆኑት ኢስማኤል ሳንቼዝ ካስቲሎ ተናግረዋል።

ለሳንቼዝ ካስቲሎ፣ ይህ ውሳኔ የሰላምን ትርጉም የሚያዛባ ሲሆን፣ የዓለም አንድነት ምልክት የሆነውን ሽልማት ወደ የፖለቲካ መጠቀሚያነት የሚቀይር ነው።

ማቻዶ “የጎዳና ላይ ዓመፅን ያበረታቱ፣ በገዛ አገራቸው ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን እንዲጣል የጠየቁ እንዲሁም በይፋ የውጭ ጣልቃ ገብነትን እንዲኖር ጥያቄ ያቀረቡ” ናቸው፤ ለሳቸው ክብር መስጠት የመሰል መዘዞች ዳፋ ሲቋቋም ለኖረው የቬንዙዌላ ሕዝብ ቀጥተኛ ንቀት ነው ሲሉ ይሞግታሉ።

“እሳቸው የመደብ ጥላቻን፣ ለድሆች ንቀትን፣ ለአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ሲባል ብሔራዊ ሉዓላዊነትን መካድን እና የልሂቃንና አግላይ የሆነውን አሰራርን ማስቀጠልን ይወክላሉ” ሲሉ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ሳንቼዝ ካስቲሎ፣ የቬንዙዌላ ሕዝብ አሁንም መድኃኒት፣ አስፈላጊ ሸቀጦች እና ምግብ የማግኘት ዕድሉን ገድበውበት በነበሩ ማዕቀቦች ትዝታ ውስጥ እየኖረ እንደሆነ ጠቁመዋል።

“እነዚህ የተከሰቱት በተፈጥሮ አደጋ ወይም  በአስተዳደር ስህተት ምክንያት አይደለም፤ ይልቁንስ ለአገራቸው በሕዝቡ የተመረጠውን ሉዓላዊ መንገድ ከመቀበል ይልቅ እንድትሽመደመድ በመረጡት እንደ ማቻዶ ባሉ ግለሰቦች የተቀየሱ ስትራቴጂ ውጤት ናቸው” ብለዋል።

ሳንቼዝ ካስቲሎ፣ ማቻዶን እንደ “የሰላም ሴት” አድርጎ ማሳየቱ “በላቲን አሜሪካ ባሉ የነፃነት ሂደቶች ላይ የሚካሄድ የምልክትና የባህል ጦርነት” አካል መሆኑን አስጠንቅቀዋል፡፡ ይህም ወግ አጥባቂ ልሂቃንን ለማፅዳትና ሉዓላዊነታቸውን የሚከላከሉ አገራትን ወንጀለኛ አድርጎ ለማቅረብ የሚደረግ ጥረት ነው ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0