በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ ወደ እንዲገቡ መወሰኑን ገንዘብ ሚኒስትር አስታወቀ
13:21 11.10.2025 (የተሻሻለ: 13:34 11.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ ወደ እንዲገቡ መወሰኑን ገንዘብ ሚኒስትር አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ ወደ እንዲገቡ መወሰኑን ገንዘብ ሚኒስትር አስታወቀ
ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዝ የማምረት ሥራ በይፋ መጀመሯን ለአዲሱን መመሪያ መውጣት እንደምክንያት ጠቅሷል።
ሚኒስቴሩ ውሳኔውን አስመልክቶ ለጉምሩክ ኮሚሽን ባስተላለፈው መመሪያ “ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በተፈጥሮ ጋዝ የሚሠሩ ማናቸውም አይነት የደረቅ እና የፈሳሽ ችነት ተሽከርካሪዎች እና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነጻ ሆነው ወደ አገር እንዲገቡ መፈቀዱን እንገልጻለን፡፡” ብሏል፡፡
“ለነዳጅ ግዥ የምናወጣውን የውጭ ምንዛሪ የሚያስቀር በመሆኑ መንግሥት የተፈጥሮ ጋዝ አጠቃቀምን ለማበረታታት ወስኗል” ሲል ነው ገንዘብ ሚኒስቴር የገለፀው፡፡ ፡
ይህ መመሪያ ከወጣበት ቀን በፊት ወደ አገር እንዲገቡ ከተፈቀደላቸው እንዲሁም በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ አገር ከሚገቡት በስተቀር በቤንዚን እና ናፍታ የሚሠሩ የጭነትና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር እንዳይገቡ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግም አሳስቧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ከቀረጥ ነጻ ወደ እንዲገቡ መወሰኑን ገንዘብ ሚኒስትር አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia
/