ቡርኪና ፋሶ ግዙፍ ኩባንያዎች መሠረታቸው አገሪቱ ውስጥ እንዲተክሉ ማቀዷን ባለሥልጣኑ አስታወቁ
20:30 10.10.2025 (የተሻሻለ: 20:34 10.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቡርኪና ፋሶ ግዙፍ ኩባንያዎች መሠረታቸው አገሪቱ ውስጥ እንዲተክሉ ማቀዷን ባለሥልጣኑ አስታወቁ
"የኩባንያዎችን የአገር ውስጥ መሠረት ማጠናከር" የሚል ረቂቅ ሕግ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቋል ሲሉ የመንግሥት ቃል- አቀባይ ፒንግድዌንዴ ጊልበርት ኦዌድራጎ ተናግረዋል።
"ባለፉት ሦስት ዓመታት አማካይ ዓመታዊ ገቢያቸው 5 ቢሊዮን የሲኤፍኤ ፍራንክ (8.8 ሚሊዮን ዶላር) የደረሰ ኩባንያዎች ዋና መሥሪያ ቤታቸውን በቡርኪና ፋሶ እንዲገነቡ ይገደዳሉ" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ንግዶችን ለማበረታታት የታቀዱ እርምጃዎች፦
በግንባታ ቁሳቁሶች ላይ የግብር ቅነሳ፣
የድርጅት ማቋቋሚያ ፕሮጀክታቸውን ለማስገባት የስድስት ወራት ጊዜ እና
በአጭር ጊዜ የሕንፃ ፈቃድ መስጠት ናቸው።
ረቂቅ ሕጉ በሽግግር የሕግ አውጪ ምክር ቤት ይመረመራል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X