የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ 'ከፋይናንስ ተቋም በላይ ነው' - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ 'ከፋይናንስ ተቋም በላይ ነው' - ባለሙያ
የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ 'ከፋይናንስ ተቋም በላይ ነው' - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.10.2025
ሰብስክራይብ

የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ 'ከፋይናንስ ተቋም በላይ ነው' - ባለሙያ

ባንኩ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ አገራት የወሳኝ የካፒታል ምንጭ እየሆነ መምጣቱን አንትሮፖሎጂስቱ መሐመድ አወል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ፡፡

"ስለ ብሪክስ ስንነጋገር መነሳት ያለባቸው ብዙ ጉዳዮች አሉ። ከሁሉ የላቀው ምሳሌ ደግሞ ሁላችንም የምናውቀው አዲስ የልማት ባንክ ነው፡፡ ይህ ባንክ ከፋይናንስ ተቋም በላይ ነው፤ ባንኩ የደቡባዊ ዓለም የራሱን የፋይናንስ ተቋማት የማስኬድ ሉዓላዊነትን ወይም አቅምን ያሳያል።” ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የብሪክስ አስተሳሰብ ከኅብረተሰቡ የመነጨ እና የአፍሪካን እንዲሁም የደቡባዊውን ዓለም ፍላጎት የሚያስቀድም ነው ፤ ነገር ግን አካሄዱ አምባገነናዊው አይደለም ሲሉ  ይሞግታሉ፡፡

"አማራጭ የፋይናንስ ፕሮግራም እና የፋይናንስ ተቋም እንዲሁም አማራጭ የፖለቲካ ንቅናቄ ማዕከል እያስተዋወቁ ነው። ስለዚህ በትንሹ ለእኔ ውጤታማ ናቸው ብዬ አስባለሁ" ሲሉ የብሪክስ መሥራቾች የሆኑት ኃያላን አገራት ለዓለም የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥተዋል።

አክለውም "የዶላር የበላይነት በእጅ አዙር ቅኝ ግዛትን ለማስቀጠል ከሚረዱ መንገዶች አንዱ ነው" በማለት ገልፀውታል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0