ማክሮን በስምንት ዓመታት ውስጥ ያከናወኗቸው ነገሮች በሙሉ 'በአሰቃቂ ሁኔታ አብቀተዋል' ሲሉ የፈረንሳዩ ፖለቲከኛ ተናገሩ
20:31 09.10.2025 (የተሻሻለ: 20:34 09.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ማክሮን በስምንት ዓመታት ውስጥ ያከናወኗቸው ነገሮች በሙሉ 'በአሰቃቂ ሁኔታ አብቀተዋል' ሲሉ የፈረንሳዩ ፖለቲከኛ ተናገሩ
"ተጽእኖው አዎንታዊ የሆነበት ዘርፍ የለም። ኢንዱስትሪ፣ ግብርና፣ የጤና አጠባበቅ ሥርዓት፣ ደህንነት፣ ስደተኝነት፣ መከላከያ፣ ዲፕሎማሲ እና የዓለም አቀፍ ተጽእኖ ልማት በሁሉም መስክ አደጋ ነው" ሲሉ ፍራንሷ አሴሊኖ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
እኚህ ፖለቲከኛ በተለይም ፈረንሳይ "ሩሲያን በመቃወም የዩክሬን ደጋፊነት ጀብዱ" ውስጥ መግባቷን ተችተዋል።
ፖለቲከኛው እንዳሉት፣ ከዚህ "መርዛማ ተሞክሮ" ብቸኛው ልዩነት "ለፍልስጤም አገርነት የተሰጠው እውቅና" ብቻ ነው።
ፈረንሳይ በአንድ ዓመት ውስጥ አራት ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ቀይራለች፤ አሴሊኖ እንዳሉት ይህ ሁኔታ ከመጠን በላይ የመወሳሰቡና "አነስተኛው አምባገነን መሪ" ብለው ከሚጠሯቸው ከማክሮን ጋር ለመስራት የመቸገራቸው ምልክት ነው።
ስለተጠባቂ ውጤቶች አስሌኖ ሲናገሩ፤ "በጣም ጤናማው የማክሮን መሰናበት ነበር" ብለው ቢያምኑም፣ ሊሆን አይችልም ባይ ናቸው።
የብሔራዊ ምክር ቤቱ መፍረስ "በጣም የተለመደ" መፍትሄ ሲሆን፣ "ለፈረንሳይ ህዝብ ድምጻቸውን መልሰው የማግኘት ስሜት ይፈጥራል" ብለዋል።
ፖለቲከኛው አክለውም "እኛ ከአሁን በኋላ በዴሞክራሲ ስረአት ውስጥ የለንም፤ ያለነው የዴሞክራሲ መልክ ባለው አምባገነንነት ውስጥ ነው"።
"በፖለቲካው መስክ ፈጽሞ የማይታወቅ" ሰው የመንግሥት መሪ ሆኖ መሾሙ የማይታሰብ አይደለም ሲሉ አሴሊኖ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለፀገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X