የብራና ሥራ ታሪክ እና ሃይማኖትን ከማስተማር ባለፈ የወጣቶችን የተበተነ ትኩረት ይመልሳል - የሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት

ሰብስክራይብ

የብራና ሥራ ታሪክ እና ሃይማኖትን ከማስተማር ባለፈ የወጣቶችን የተበተነ ትኩረት ይመልሳል - የሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት

የድርጅቱ ዳታ አናሊስት ጽዮን ጌታቸው፣ የብራና ሥራ ከመንፈሳዊ እሴቱ ባሻገር በማኀበራዊ ትስስር ገጾች የተጠመደ የወጣቶችን አዕምሮ ለመሰብሰብ እና የእጅ ሙያ ለማስተማር የላቀ እገዛ እንዳለው ትናገራለች።

"እዚህ መጻሕፍትን ጨምሮ አብዛኛዎቹ ነገሮች የሚሰሩት በእጅ ነው። ይህም በስክሪን በኩል የምዕራቡ ዓለም በወጣቶች አዕምሮ ላይ ለማተም ከሚሞክራቸው እሳቤዎች ራቅ ብለን እጃችንን ለማፍታታት ይጠቅመናል።" ብላለች።

ጽዮን ጌታቸው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራት ቆይታ ድርጅቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያንን ቅርስ፣ ጥበብ እና አስተምሕሮ ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ለማቆየት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትንም አውስታለች።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0