የአዘርባጃን አውሮፕላን አደጋ መንስኤዎች ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ በሰማይ ላይ ከነበረው የዩክሬን ድሮን ጋር የተያያዙ ናቸው - ፑቲን
17:13 09.10.2025 (የተሻሻለ: 17:14 09.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአዘርባጃን አውሮፕላን አደጋ መንስኤዎች ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ በሰማይ ላይ ከነበረው የዩክሬን ድሮን ጋር የተያያዙ ናቸው - ፑቲን
የሩሲያው ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ አገራቸው በነባር ስምምነቶች መሠረት በአዘርባጃን አውሮፕላን አደጋ ምርመራ ላይ ሙሉ በሙሉ እየተባበረች መሆኑን ገልጸዋል።
'ኢምብራየር 190' ተብሎ የሚጠራው የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን ባለፈው ዓመት ታኅሣሥ 16 ከባኩ ወደ ግሮዝኒ ሲበር፤ በምዕራብ ካዛክስታን አቅራቢያ በምትገኘው አክታው ከተማ አቅራቢያ መከስከሱ ይታወሳል።
አውሮፕላኑ ለማረፍ በዝግጅት ላይ እያለ፣ የዩክሬን አሸባሪዎች ካሚካዜ ድሮኖችን በመጠቀም በቼቼን ሪፐብሊክ የሚገኘውን የግሮዝኒ እና በሰሜን ኦሴቲያ ሪፐብሊክ የሚገኘውን የቭላዲካቭካዝ ሲቪል መሠረተ ልማት መምታታቸውን ተከትሎ፣ የሩሲያ የአየር መከላከያ ሥርዓቶች እነዚህን ጥቃቶች እየመከቱ ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X