የኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ እድገትና የኃይል ውህደት ቁልፍ አንቀሳቃሽ ነው - ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ
15:55 09.10.2025 (የተሻሻለ: 16:04 09.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ እድገትና የኃይል ውህደት ቁልፍ አንቀሳቃሽ ነው - ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ
የሶማሊያው መሪ፣ የ5 ሺህ ሜጋዋት ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የተገኘ “ስኬታማ ውጤት” ነው ሲሉ ተሳትፎ ካደረጉበት የግድቡ ምረቃ በኋላ ከአል-አረቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል።
"ግድቡ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና በሰፊው ክልል ላይ በአዎንታዊ መልኩ ተፅእኖ ይፈጥራል" ያሉ ሲሆን ኃይል ደግሞ "ለማንኛውም ልማት በጣም አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ" መሆኑን አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ቀደም ሲልም ለኬንያ፣ ሱዳን እና ጅቡቲ ኤሌክትሪክ እንደምትልክ ጠቅሰው፣ የፕሮጀክቱን እያደገ የመጣ ቀጣናዊ ጠቀሜታ አጉልተዋል።
ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ አገራቸው ግድቡን በተመለከተ የጋራ እና የተረጋጋ መፍትሄ ለማረጋገጥ ሱዳን እና ከግብፅን ጨምሮ ከሚመለከታቸው ሁሉም አገራት ጋር የሚደረግ ውይይትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X