ኢትዮጵያ በአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና በይፋ መገበያየት ጀመረች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አኅጉራዊ ነጻ ንግድ ቀጣና በይፋ መገበያየት ጀመረች

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ካርጎ ተርሚናል ተገኝተው ግብይቱን በማስመልከት የተዘጋጀውን መርሀ ግብር በይፋ አስጀምረዋል።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩን ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ፣ "የስምምነቱ ተግባራዊ መሆን ቀድሞውኑ በትክክለኛ ትራክና ዕድገት ላይ እየመጣ ያለውን የሀገራችን የወጪ ንግድ በማሳለጥ ረገድ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ይታሰባል" ብለዋል።

ተጭነው ዛሬ ከተላኩና ከሚላኩ ምርቶች መካከል፦

ስጋ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ጫት ወደ ሶማሊያ

ነጭና ቀይ ቦሎቄ እንዲሁም ቡና ደቡብ አፍሪካ

የበቆሎና የቦሎቄ ምርቶች ወደ ኬንያ

ስምምነቱ ሊተገበር ከታሰበበት ጊዜ ጀምሮ በአንድ ነጋዴ ደረጃ በቆሎ ወደ ኬንያ በመላክ ብቻ 7 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ20 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ ኮንትራት መያዙን ዶ/ር ካሳሁን መግለጻቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0