አውሮፓ በዕዳ ቀውስ አፋፍ ላይ ስትሆን፤ ፈረንሳይ እና ኢጣሊያ ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸውን የሮስኮንግረስ ሪፖርት አስጠነቀቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአውሮፓ በዕዳ ቀውስ አፋፍ ላይ ስትሆን፤ ፈረንሳይ እና ኢጣሊያ ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸውን የሮስኮንግረስ ሪፖርት አስጠነቀቀ
አውሮፓ በዕዳ ቀውስ አፋፍ ላይ ስትሆን፤ ፈረንሳይ እና ኢጣሊያ ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸውን የሮስኮንግረስ ሪፖርት አስጠነቀቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.10.2025
ሰብስክራይብ

አውሮፓ በዕዳ ቀውስ አፋፍ ላይ ስትሆን፤ ፈረንሳይ እና ኢጣሊያ ከፍተኛ አደጋ ላይ መሆናቸውን የሮስኮንግረስ ሪፖርት አስጠነቀቀ

አውሮፓ በቅርቡ ዓለም አቀፉን የፋይናንስ ሥርዓትን ሊያናውጥ በሚችል የዕዳ ቀውስ ሊገጥማት እንደሚችል፣ ስፑትኒክ የተመለከተው የሮስኮንግረስ "የበጀት  አዲስ ሪፖርት አመላከተ።

ስፑትኒክ ያየው የሮስኮንግረስ “የበጀት አለመመጣጠን እና የአውሮፓ ሕብረት የዕዳ ወጥመድ” የተሰኘ አዲስ ሪፖርት ገልጿል።

“የበጀት አለመመጣጠን እና የአውሮፓ ሕብረት የዕዳ ወጥመድ” የተሰኘው ሪፖርት ቁልፍ ግኝቶች የሚከተሉት ናቸው ፦

▪ ማንም ዋና የአውሮፓ አገር ላለፉት 40 ዓመታት “የቦውን መርህ”ን አልተከተለም፤ ይህ መርህ የዕዳን መጠን ለማረጋጋት ያለፉት የዕዳ ጭማሪዎች አሁን ወይም ወደፊት በሚገኝ የበጀት ትርፍ እንዲካካሱ የሚጠይቅ ነው።

▪  ምንም እንኳን ጥብቅ የበጀት ቁጥጥር ቢደረግም፤ በጎርጎሮሳዊያኑ 2008 ያጋጠመው ቀውስ ወይም እንደ ወረርሽኝ ባሉ የዕዳ ድንጋጤዎች ምክንያት ከሚፈጠረው ችግር ለማገገም እስከ 20 ዓመታት የሚደርስ ከፍተኛ የበጀት ትርፍ ያስፈልጋል።

ወጪን መቀነስ ወይም ግብር መጨመር ? ሁለቱም ዝግ ናቸው።

▪  የግብር ምጣኔዎች አስቀድመው በጣም ከፍተኛ ስለሆኑ (ለምሳሌ በፈረንሳይ)፣ ተጨማሪ ጭማሪ ገቢን ከመጨመር ይልቅ ይቀንሳል።

▪ ከፍተኛ ግብሮች የኢንቨስትመንት እና የሥራ ዕድል ማበረታቻዎችንም ያዳክማሉ።

በጂኦፖለቲካዊ መከፋፈል፣ በውስጣዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት እና በተዳከመ የውጭ ፍላጎት በተለይም ከአሜሪካ አዲስ ቀረጥ የተነሳ የአኅጉሪቱ የዕድገት አቅም እየደበዘዘ መሆኑን ሪፖርቱ ጠቁሟል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0