1⃣ የጋዛ ሰላም እቅድ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቀቀ፡ እስካሁን የታወቀው ነገር ምንድን ነው?

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ1⃣ የጋዛ ሰላም እቅድ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቀቀ፡ እስካሁን የታወቀው ነገር ምንድን ነው?
1⃣ የጋዛ ሰላም እቅድ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቀቀ፡ እስካሁን የታወቀው ነገር ምንድን ነው? - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.10.2025
ሰብስክራይብ

1⃣ የጋዛ ሰላም እቅድ የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቀቀ፡ እስካሁን የታወቀው ነገር ምንድን ነው?

እስራኤል እና ሃማስ በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማቆም በቀረበው የዶናልድ ትራምፕ የሰላም ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ተስማምተዋል፡፡

የትራምፕ የሰላም እቅድ የመጀመሪያ ምዕራፍ የተኩስ አቁም እና በጋዛ ታስረው የሚገኙ 48 እስራኤላውያን ታጋቾችን መለቀቅ የሚያካትት ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ 20 የሚሆኑት በሕይወት እንዳሉ ይታመናል ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ታጋቾቹ ጥቅምት 3፣ 2018  ሊለቀቁ እንደሚችሉ ትራምፕ ተናግረዋል።

የእቅዱ የመጀመሪያ ምዕራፍ በእስራኤል እስር ቤቶች ታስረው የሚገኙ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ፍልስጤማውያን እስረኞችን መለቀቅንም ያካትታል።

ትራምፕ በትሩዝ የማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስነበቡት፣ እስራኤል ወታደሮቿን ከእቅዱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ጋር በተጣጣመ መልኩ ወደተስማሙበት መስመር ታስወጣለች።

ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሰጡት ምላሽ

  ትራምፕ ስምምነቱን “ወደ ጠንካራ፣ ዘላቂ እና የማይጠፋ ሰላም የሚወስድ የመጀመሪያ እርምጃ” ሲሉ አሞካሽተውታል።

  የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ስምምነቱን ለአገራቸው “ዲፕሎማሲያዊ ስኬት እንዲሁም ብሔራዊና ሞራላዊ ድል” ሲሉ ገልጸውታል።

  ሃማስ በስምምነቱ የተሳተፉትን ትራምፕን ጨምሮ እንደ ኳታር፣ ግብፅ እና ቱርክ ያሉትን የመካከለኛ ምስራቅ አደራዳሪዎች በሙሉ አመስግኗል። ስምምነቱ የመጣውም በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ሐሳብ ላይ "ትክክለኛ እና ኃላፊነት የተሞላበት ድርድር" ከተደረገ በኋላ መሆኑን አጽንዖት ሰጥቷል።

  የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ስምምነቱን በደስታ የተቀበሉ ሲሆን፣ ሁሉም ተዋዋይ ወገኖችም የስምምነቱን ውሎች “በሙሉ እንዲያከብሩ” አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0