ሩሲያ እና ታጂኪስታን ታማኝ አጋሮች ናቸው፤ ሞስኮ ለግንኙነቶቹ ከፍተኛ ትኩረት ትሰጣለች - ፑቲን
10:58 09.10.2025 (የተሻሻለ: 11:04 09.10.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ እና ታጂኪስታን ታማኝ አጋሮች ናቸው፤ ሞስኮ ለግንኙነቶቹ ከፍተኛ ትኩረት ትሰጣለች - ፑቲን
የሩሲያ እና የታጂኪስታን ፕሬዝዳንቶች በዱሻንቤ የአንድ ለአንድ ንግግራቸው ወቅት የተሰጡ ቁልፍ መግለጫዎች፦
ቭላድሚር ፑቲን
በሩሲያ እና በታጂኪስታን መካከል ያለው ግንኙነት በሁሉም ዘርፎች በአዎንታዊ መልኩ እያደገ ነው።
ሩሲያ እና ታጂኪስታን ከቀጣናዊ ሁኔታው ጋር በሚጣጣም መልኩ በመከላከያ እና ደህንነት ዘርፎች ያለማቋረጥ ይተባበራሉ።
ኢሞማሊ ራሕሞን
በሩሲያ እና በታጂኪስታን መካከል ያለው ግንኙነት እያደገ መሆኑን እና ሁለቱ ወገኖች የማያቋርጥ የፖለቲካ ውይይት ማድረጋቸውን ማየት የሚያበረታታ ነው።
ሩሲያ እና ታጂኪስታን ንግዳቸው እያደገ፣ የደህንነት ትብብራቸውንም እያሰፉ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X