የሩሲያ የኬሚካል መከላከያ ዋና አዛዥን ለመግደል በጎርጎሮሳዊያኑ 2024 ጥቅም ላይ የዋለው ፈንጂ ክፍሎች ከፖላንድ መላካቸውን መርማሪዎች ገለጹ
21:31 08.10.2025 (የተሻሻለ: 21:34 08.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ የኬሚካል መከላከያ ዋና አዛዥን ለመግደል በጎርጎሮሳዊያኑ 2024 ጥቅም ላይ የዋለው ፈንጂ ክፍሎች ከፖላንድ መላካቸውን መርማሪዎች ገለጹ
የሩሲያ የጦር ኃይሎች የጨረር፣ የኬሚካልና የባዮሎጂካል መከላከያ ጦር ዋና አዛዥ ሌተናንት ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭን የገደለው የሽብር ጥቃት አቀነባባሪዎች የተሻሻለውን የፈንጂ ክፍሎች ተራ የቤት እቃዎች አስመስለው መላካቸውን የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ ለስፑትኒክ አስታውቋል።
የምርመራ ኮሚቴው በአራቱ ወንጀለኞች የተፈጸመው የታህሳስ ወር የሽብር ጥቃት ምርመራ ተጠናቋል ሲል በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።
ኪሪሎቭ እና ረዳታቸው የተገደሉት ታህሳስ 2017 ዓ.ም በሞስኮ በሚገኘው የመኖሪያ ሕንፃቸው መግቢያ አጠገብ ቆሞ በነበረ ስኩተር ውስጥ ተደብቆ በነበረ ፈንጂ አማካኝነት መሆኑ ይታወሳል።
ኮሚቴው በመግለጫው “በማዕከላዊ ቢሮ የሚገኙ ከፍተኛ መርማሪዎች ወንጀሉ ዩክሬን ውስጥ በጥንቃቄና በሰፊው መታቀዱን አረጋግጠዋል” ብሏል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ መኮንኑ በተገደሉበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ኪሪሎቭ “የአንግሎ-ሳክሶን እና የኔቶ ቅስቀሳ ወንጀሎችን በስልታዊ መንገድ ያጋልጥ የነበረ ሲሆን፣ ያለ ፍርሃትም ይሠራ ነበር”።
ሟቹ ሌተናንት ጄኔራል በአፍሪካ ስላለው "ባዮሎጂካል" ደህንነት እና የምዕራቡ ዓለም በአኅጉሪቱ ስላለው ባዮሎጂካል እንቅስቃሴዎች በተመለከተም በተደጋጋሚ ሪፖርት አድርገው ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X