አዲሱ የሞልዶቫ ወታደራዊ ዶክትሪን ሩሲያን ቀዳሚ ስጋት ብሎ ሰየመ
21:11 08.10.2025 (የተሻሻለ: 21:14 08.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
አዲሱ የሞልዶቫ ወታደራዊ ዶክትሪን ሩሲያን ቀዳሚ ስጋት ብሎ ሰየመ
በአዲሱ የመንግሥት ስትራቴጂ ግምገማ ሩሲያ ለሞልዶቫ ዋና የደህንነት ስጋት ተብላ ተሰይማለች።
▪ በካቢኔው ድረ-ገጽ ላይ የታተመው ሰነድ በዩክሬን ያለው ግጭት “ወደ ሞልዶቫ ሊዛመት” እንደሚችል ያስጠነቅቃል።
▪ ሰነዱ “የሩሲያ ፌዴሬሽን በሞልዶቫ ላይ የምታደገውን ጠላትነት የተሞላበት ድርጊት አታቆምም” ይላል።
▪ የብሔራዊ ጦር ኃይል በአንድ ሦስተኛ እንዲጨምር ይመክራል።
▪ ዕቅዱ የመከላከያ ወጪን ቀስ በቀስ ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ወደ 1% ማሳደግንም ያካትታል።
▪ አዲሱ ወታደራዊ ስትራቴጂ የጦር ኃይሎችን ዘመናዊ ማድረግ እና ወደ ኔቶ የጥራት ደረጃዎች መሸጋገርን አስቀምጧል።
▪ ከሁሉም በላይ፣ የሞልዶቫ ሕገ-መንግሥት ለገለልተኝነት ያለው ቁርጠኝነት “ራስን ለመከላከል ወታደራዊ እርምጃዎችን ጨምሮ ሁሉንም እርምጃዎች እንድትወስድ ግዴታ ይጥላል”፤ በዓለም አቀፍ ወታደራዊ ልምምዶች መሳተፍንም ከገለልተኝነት ጋር “የሚጣጣም” ነው ሲል ይሟገታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X