ኤርትራ እና ሕወሓት "ፅምዶ" ባሉት የጋራ ጥምረት ስር የጦርነት ሴራ እየሸረቡ ነው ስትል ኢትዮጵያ ከሰሰች

ኤርትራ እና ሕወሓት "ፅምዶ" ባሉት የጋራ ጥምረት ስር የጦርነት ሴራ እየሸረቡ ነው ስትል ኢትዮጵያ ከሰሰች
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ለተመድ ዋና ፀሐፊ በጻፉትና ሚዲያዎች ባዩት ደብዳቤ፤ በኤርትራ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል ያለው “ሴራ” ባለፉት ጥቂት ወራት “ይበልጥ ግልጽ ሆኗል” ብለዋል።
ሁለቱም ወገኖች "ፋኖን የመሰሉ የታጠቁ ቡድኖችን፣ በገንዘብ በመደገፍ፣ በማንቀሳቀስና በመምራት የግጭቱን አድማስ በማስፋት" በ"ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ለመክፈት በንቃት እየተዘጋጁ ነው” ሲሉ እንደጻፉ ተዘግቧል።
🪖 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርትራና ሕወሓት በቅርቡ የአማራ ክልልን ከተማ ወልዲያን ለመያዝ በተደረገው የፋኖ ጥቃት ድጋፍ በማድረግ፣ እንዲሁም በራያ እና በወልቃይት አካባቢ በሚደረገው ውጊያ ውስጥ በመሳተፍ እ.አ.አ. በ2022 የተፈረመው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተጥሷል ሲል ከስሷል።
ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ኤርትራን “የእነዚህ አስከፊ ተግባራት ዋና አቀናባሪ” በማለት የገለጿት ሲሆን፣ አስመራ የድርጊቷን ልክነት የምታስረዳው “የኢትዮጵያ ወደብ የማግኘት ፍላጎት ማስፈራሪያ ሆኖብኛል በሚል ሽፋን ነው” ብለዋል።
ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ወደብ ማግኘትን የምትፈልገው “በሰላማዊ መንገድ” እንደሆነና “በቅን ልቦና ለሚደረግ ድርድር” ዝግጁ እንደሆነች አረጋግጠዋል።
ℹ እ.ኤ.አ. የ2018ቱ የሰላም ስምምነት (ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል ሽልማት ያስገኘላቸው) ከቀዘቀዘ በኋላ ለአጭር ጊዜ ተሻሽሎ የነበረው የሁለቱ ጎረቤታሞች ግንኙነት፣ በቀይ ባሕር ወደብ የማግኘት ፍላጎት እና በተባባሰው ድንበር ተሻጋሪ ጠብ አጫሪነት ምክንያት እንደገና መበላሸቱ ታውቋል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X