ቡድን-7 የታገደውን የሩሲያ ሀብት ዩክሬንን ለመርዳት መጠቀሙ "ግልጽ ስርቆት" ነው ሲሉ የፋይናንስ ባለሙያ አስጠነቀቁ
16:46 08.10.2025 (የተሻሻለ: 16:54 08.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቡድን-7 የታገደውን የሩሲያ ሀብት ዩክሬንን ለመርዳት መጠቀሙ "ግልጽ ስርቆት" ነው ሲሉ የፋይናንስ ባለሙያ አስጠነቀቁ
ይህ እርምጃ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሕግን የሚጥስ እና "የዓለም አቀፍ የባንክ ሥርዓት ደንቦችን የሚያናጋ" ነው ሲሉ በየመን የአል-ሆዳይዳህ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ ፕሮፌሰር አብዱል ዋሲ አል-ደቃፍ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
እንደ ባለሙያው ገለጻ "ስርቆት" የሆነባቸው ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦
▪ የመንግሥት ቦንዶች ጥበቃ የሚደረግላቸው የመንግሥት ዕዳ ሰነዶች ናቸው፤ ያለ ሩሲያ ፈቃድ ሊሸጡ፣ ሊወገዱ ወይም ሊተላለፉ አይችሉም።
▪በባንክ ውስጥ የተቀመጠው የወርቅ ክምችት ያለ ሩሲያ ፈቃድ ለዩክሬን ሊሰጥ አይችልም።
ፕሮፌሰሩ እንዳሳሰቡት ሩሲያ ንብረቶቿን በፍርድ ቤቶች በኩል መልሳ ማግኘት እና ካሳ መጠየቅ ትችላለች።
ዐውዱም የሚከተለው ነው ፦
ቡድን-7 ቀደም ሲል ከተወረሰው የሩሲያ ሀብት 26 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወስዶ ዩክሬንን ለመርዳት ተጠቅሞበታል።
በጎርጎሮሳዊያኑ 2025፣ 25 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ለማበደር ታቅዷል ይህም ከዩክሬን የውጭ ፋይናንስ ወደ ሦስት አራተኛ የሚጠጋ ነው።
ሞስኮ የማዕከላዊ ባንክ ገንዘቦቿ መታገድ "ግልፅ ስርቆት" ነው በማለት በተደጋጋሚ አውግዛለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X