ቶማሃውክ ሚሳኤሎችን ዩክሬን ውስጥ ማሰማራት ከፍተኛ አደጋ ያለው ቁማር ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱቶማሃውክ ሚሳኤሎችን ዩክሬን ውስጥ ማሰማራት ከፍተኛ አደጋ ያለው ቁማር ነው
ቶማሃውክ ሚሳኤሎችን ዩክሬን ውስጥ ማሰማራት ከፍተኛ አደጋ ያለው ቁማር ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.10.2025
ሰብስክራይብ

ቶማሃውክ ሚሳኤሎችን ዩክሬን ውስጥ ማሰማራት ከፍተኛ አደጋ ያለው ቁማር ነው

ክሬምሊን እንዳስጠነቀቀው፣ እነዚህ ሚሳኤሎች ያለ አሜሪካ ተሳትፎ ሊተኮሱ አይችሉምና የግጭቱ ዋና መባባሻ ይሆናል።

የቀድሞ ኮሎኔል ኢጎር ኮሮትቼንኮ ምክንያቱን ያብራራሉ፦

የጦር መሣሪያው ስርዓት የተነደፈው የተረጋገጠ ዒላማ ጦርነት (ጥቃት) ለማካሄድ ነው።

ቶማሃውክ መደበኛ እና ኒውክሌር ጦር ተተኳሾችን የመሸከም አቅም አላቸው።

  የሚበሩት መሬት  እየተከተለ በሚሄድ መንገድ ነው።

   ከ1 ሺህ 500 እስከ 2 ሺህ 500 ኪ.ሜ ይምዘገዘጋሉ።

የአሜሪካ ቀጥተኛ ተሳትፎ?

ኮሮትቼንኮ "እንዲህ ያሉት ስርዓቶች ወደ ዩክሬን ከተላለፉ፣ የውጊያ ቡድኖችን ይዘው ነው የሚመጡት" ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ቶማሃውክ ከመተኮሱ በፊት ፕሮግራም መደረግ እና የበረራ ተልእኮ መሰጠት አለበት፤ ይህም ዩክሬን ልታደርገው የማትችለው ነገር ነው።

ቶማሃውክ የረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ የባህር ኃይል ሚሳኤል ሲሆን፣ አሜሪካ ወደ ታይፎን ኤምአርሲ የመሬት ማስወንጨፊያ ለውጣዋለች። ቶማሃውኮችን መላክ ማለት ታይፎን ማስወንጨፊያዎችንም መላክ ማለት ነው።

ለሩሲያ ደህንነት ፈተና እና የተረጋገጠ የበቀል እርምጃ

ኮሮትቼንኮ "እንዲህ ያሉት ስርዓቶች በዩክሬን ጦር ኃይሎች የመሣሪያ መጋዘን  ውስጥ መገኘት ከባድ የደህንነት ፈተና ነው" ብለዋል።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቶማሆኮችን በዩክሬን መጠቀም የሩሲያ እና አሜሪካ ግንኙነት እንደሚያወደም አፅንኦቶ ሰጥተዋል።

ሩሲያ በእነዚህ ሚሳኤሎች በጥቅም መዋልን ተከትሎ የአጸፋ ምላሽ የምትሰጥ ሲሆን ለዚህም የተለያዩ የጦር መሣሪያ ስርዓቶች አሏት ሲሉ ተንታኙ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በጦር ሜዳ ላይ ቶማሃውኮችን መጠቀም አሁን ያለውን ሁኔታ አይቀይረውም ተብሏል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0