ኢትዮጵያና ፓኪስታን የመከላከያ እና የአቪዬሽን ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያና ፓኪስታን የመከላከያ እና የአቪዬሽን ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
ኢትዮጵያና ፓኪስታን የመከላከያ እና የአቪዬሽን ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያና ፓኪስታን የመከላከያ እና የአቪዬሽን ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

መሰል ስምምነቶች የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚደረጉ ጥረቶች አካል መሆናቸውን በኢዝላማባድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ሀገራቱ ስምምነት ላይ የደረሱት መስከረም 26፣ 2018 ዓ.ም በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ጀማል በከር ከፓኪስታን የመከላከያ ሚኒስትር ክዋጃ አሲፍ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

እንደ ኤምባሲው መግለጫ ውይይቱ፦

በሰላምና ደኅንነት፣

መከላከያ፣

አቪዬሽን፣

የአየር ንብረት ለውጥ፣

ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም

ባህልና ቱሪዝምን ጨምሮ በተለያዩ የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ትብብር መስኮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።

አምባሳደሩ ከካራቺ በተጨማሪ ወደ ሌሎች የፓኪስታን ከተሞች የበረራ መዳረሻዎችን ለማስፋፋት ፍላጎት እንዳለ ገልጸዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሩ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ለሰላም፣ ለደህንነት እና ለመረጋጋት የሚታደርገውን ቁልፍ ሚና አድንቀው፣ ፓኪስታን ለእነዚህ ጥረቶች ያላትን ጠንካራ ድጋፍ አረጋግጠዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያና ፓኪስታን የመከላከያ እና የአቪዬሽን ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
ኢትዮጵያና ፓኪስታን የመከላከያ እና የአቪዬሽን ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 08.10.2025
አዳዲስ ዜናዎች
0