ኢትዮጵያ ባለፈው የበጀት ዓመት የግብር ገቢዋን 80 በመቶ ማሳደጓን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ
15:24 08.10.2025 (የተሻሻለ: 16:24 08.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ባለፈው የበጀት ዓመት የግብር ገቢዋን 80 በመቶ ማሳደጓን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ
የተሰበሰበው ገቢ ዘጠኝ ቢሊዮን ዶላር በላይ መሆኑን ሚኒስትሯ ዐይናለም ንጉሴ በ11ኛው የአፍሪካ "ቲንክ ታንክ" ጉባኤ ላይ ገልፀዋል፡፡ ለተመዘገበዉ ዕድገት የአገሪቱ የግብር ማሻሻያዎች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል ብለዋል።
ባለፉት ስድስት ዓመታት በተተገበረው ሁለተኛው ምዕራፍ አገር አቀፍ የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ስር በግብር አሰባሰብ፣ በዕዳ አያያዝ እና በሕዝብ ፋይናንስ አስተዳደር ላይ ጉልህ ለውጦች ተደርገዋል ማለታቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግባለች።
ከቀጣናዊ መንግሥታት ጋር ከተጋራ በኋላ በተደረገው ስሌት የተጣራ የቀረጥ ገቢ ከ700 ሚሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን አጽናኦት ሰጥተዋል፡፡
በጉባኤው ላይ በመላው አኅጉሪቱ ውስጥ የሚገኙ አስቸኳይ የፋይናንስ አስተዳደር ተግዳሮቶችን ለመወያየት የተለያዩ የፖሊሲ አውጪዎች፣ ተመራማሪዎች እና የልማት አጋሮች እየተሳተፉበት ይገኛሉ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

