ኢትዮጵያ እና ኬንያ የላሙ ወደብን በተሟላ መልኩ አገልግሎት ለማስጀመር በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
14:42 08.10.2025 (የተሻሻለ: 14:44 08.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ኬንያ የላሙ ወደብን በተሟላ መልኩ አገልግሎት ለማስጀመር በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
የላሙ ወደብ የላብሴት ፕሮጀክት አካል በመሆኑ ኢትዮጵያ ወደቡ በተሟላ መልኩ አገልግሎት እንዲጀምር ፍላጎት እንዳላት የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ ደንጌ ቦሩ ከላሙ ወደብ ማናጀር ኢንጂነር አብዱላሂ ሳማታር በነበራቸው ውይይት ወቅት አንስተዋል።
አክለውም ሀገራቱ ከወደቡ ጋር የሚያገናኛቸውን የየራሳቸውን መንገድ ለመገንባት በተስማሙት መሠረት ኢትዮጵያ በራሷ በኩል ያለውን የመንገድ መሠረተ ልማት አስቀድማ ገንብታለች ማለታቸውን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።
አብዱላሂ ሳማታር በበኩላቸው፣ በኬንያ ወገን የሚገነባው የመንገድ መሠረተ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ኢትዮጵያ ወደቡን በተሟላ ሁኔታ መጠቀም እንደምትችል አስታውቀዋል።
ሀገራቱ ለዚሁ ጉዳይ የተቋቋመው የሥራ ግብረ ሃይል ሥራ እንዲጀምር ተስማምተዋል።
ኢትዮጵያ የላሙ ወደብን በመጠቀም በተለይ፦
የአፈር ማዳበሪያን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እና
የቁም እንስሳትን ለመላክ እና
ሌሎች ምርቶችን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ ፍላጎት አላት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/2
© telegram sputnik_ethiopia

2/2
© telegram sputnik_ethiopia
1/2
© telegram sputnik_ethiopia
2/2
© telegram sputnik_ethiopia