ኢትዮጵያ የአፍሪካ የጨርቃጨርቅ ዘርፍ ማዕከል የመሆን እድሉም አስቻይ ሁኔታውም አላት - የግብርና ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ የአፍሪካ የጨርቃጨርቅ ዘርፍ ማዕከል የመሆን እድሉም አስቻይ ሁኔታውም አላት - የግብርና ባለሙያ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ የጨርቃጨርቅ ዘርፍ ማዕከል የመሆን እድሉም አስቻይ ሁኔታውም አላት - የግብርና ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.10.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የጨርቃጨርቅ ዘርፍ ማዕከል የመሆን እድሉም አስቻይ ሁኔታውም አላት - የግብርና ባለሙያ

“የጥጥ ምርትን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የማምረት አቅም አለ፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የአየር ፀባይ ለጥጥ ምርታማነት ጥሩ ነው፡፡ ወጣት አምራች ሀይልም እንዲሁ በከፍተኛ ቁጥር ማግኘት ይቻላል፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ ለምሳሌ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የጨርቃ ጨርቅ ትምህርት ይሰጣል፡፡ ስለዚህ ይህ ሁሉ በአንድ ላይ የራሱ አበርክቶ ይኖረዋል” ሲሉ የግብርና ዘርፍ ባለሙያው በጋሻው መብራቴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ጥጥን እሴት በመጨመር ማምረትና በራስ አቅም ለገበያ ማቅረብ አዳዲስ የሥራ እድል እንዲፈጠርና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማደረግ ኢኮኖሚውን እንደሚያግዝ ባለሙያው ገልፀዋል፡፡

ወደ ጨርቃጨርቅ ምርት በመቀየር የሀገር ውስጥ ገበያን ብሎም የወጪ ንግዱን በእኩል ተደራሽ ማድረግ የሚቻልበት አዋጭ ስርዓት መገንባት እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0