የኢትዮጵያ ልዑክ ከናይጄሪያ የምርጫ ስርዓት ልምድ ለመውሰድ ያለመ ጉብኝት አካሄደ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ ልዑክ ከናይጄሪያ የምርጫ ስርዓት ልምድ ለመውሰድ ያለመ ጉብኝት አካሄደ
የኢትዮጵያ ልዑክ ከናይጄሪያ የምርጫ ስርዓት ልምድ ለመውሰድ ያለመ ጉብኝት አካሄደ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.10.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ ልዑክ ከናይጄሪያ የምርጫ ስርዓት ልምድ ለመውሰድ ያለመ ጉብኝት አካሄደ

ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ እና ‘ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ጥምረት ለምርጫ’ የተወጣጡ ልዑካን ለምርጫ ስርዓት ምልከታና የምርጫ አስተዳደር የልምድ ልውውጥ በናይጄሪያ የአንድ ሳምንት ቆይታ ያደርጋሉ፡፡

የናይጄሪያ ብሔራዊ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሞድ ያኩቡ፤ ከልዑካን ቡድኑ ጋር የሀገሪቱን የምርጫ ስርዓቶች ያካተተ ዘጠኝ የቴክኒክ ውይይቶች እንደሚኖራቸው ገልፀዋል፡፡

ዋነኛ የውይይቱ ትኩረቶች፦

🟠 ስትራቴጂክ እቅድ አወጣጥ፣

🟠 የምርጫ ቁጥጥር ስርዓት፣

🟠 የመራጮች ምዝገባ ቴክኖሎጂ፣

🟠 የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ፣

🟠 ተፈናቃይ ዜጎችን ማካተት፣

🟠 የመገናኛ ብዙኃን እና የፓለቲካ ፓርቲ የጋራ አመራር ልምምድ ልውውጥ፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ም/ሰብሳቢ ተስፋዬ ንዋይ፤ ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ በመራጮች ምዝገባ፣ የስነ-ዜጋ ትምህርትና ቴክኖሎጂ መር የምርጫ ሪፎርም ልምድ እንደምትወስድ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ 7ኛውን ዙር ሀገራዊ ምርጫ በተያዘው ዓመት እንደምታካሂድ ርዕሰ ብሄሩ ትናንት ማረጋገጫ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0