ሰው ሠራሽ አስተውሎት ለመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ውጤታማነት ትልቅ አቅም ነው - የዘርፉ ምሑር

ሰብስክራይብ

ሰው ሠራሽ አስተውሎት ለመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ውጤታማነት ትልቅ አቅም ነው - የዘርፉ ምሑር

የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ከዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ጋር በማቅናጀት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የመሠረታዊ ጤና አገልግሎት ተደራሽነት ማሳደግ እንደሚገባ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል ጤና እና አተገባበር ሳይንስ ፕሮፌሰር ቢንያም ጥላሁን ተናግረዋል።

"ባለሙያዎቹ በእጃቸው እየያዙት ያለውን ታብሌት አገልግሎቱን ለማሻሻል እንዴት መጠቀም እንደሚቻል ማስተማር አስፈላጊ ነው። ይህም የጤና ሽፋንን ለማሳካት የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ከፍተኛ እገዛ ይኖረዋል" ብለዋል።

ፕሮፌሰሩ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ እያሽቆለቆለ ያለውን ዓለም አቀፍ የጤና ድጋፍ ለመቋቋም ውስን ሐብቶችን በአግባቡ የመጠቀም አስፈላጊነትንም አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0