ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ ከግማሽ ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች
19:06 07.10.2025 (የተሻሻለ: 19:14 07.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ ከግማሽ ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች
በተጠቀሰው ግዜ ከ80 ሺህ ቶን በላይ ቡና ምርት ለውጭ ገበያ በማቅረብ 546 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር)፤ አርሶ አደሩ ምርቱን በቀጥታ ወደ ተለያዩ ሀገራት መላክ እንዲችል መደረጉ ለገቢው ማደግ አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ብቻ ይከናወን የነበረው የቡና ጥራት ምርመራ፤ አሁን ላይ ወደ አርሶ አደሩ አቅራቢያ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
የቡና ቅምሻ ማዕከላትን በማስፋፋት፤ የተሻለ ጥራት ያላቸው የቡና ምርቶችን ወደ ዓለም ገበያ በማቅረብ የገቢ መጠኑ ማደጉን ገልፀዋል፡፡
በ2017 በጀት ዓመት 470 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 2.26 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ያስታወሱት ኃላፊው፤ በ2018 በጀት ዓመት 600 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 3 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት መታቀዱን ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X