የጤና ዘርፍ የሀገር ውስጥ ፋይናንስን ማሳደግ አለብን - የጤና ሚኒስትር ዴኤታ

ሰብስክራይብ

የጤና ዘርፍ የሀገር ውስጥ ፋይናንስን ማሳደግ አለብን - የጤና ሚኒስትር ዴኤታ

ዶ/ር ደረጄ ድጉማ፤ የአፍሪካ መንግሥታት ከአጠቃላይ በጀታቸው ውስጥ 15 በመቶ የሚሆነውን ለጤና ዘርፍ ለማዋል ያወጡትን 'የአቡጃ መግለጫ' ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው የጤና ባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ ዘርፉን ከድጋፍ ጠባቂነት ማላቀቅ እንደሚገባም አጽዕኖት ሰጥተዋል።

"የእኛ የጤና ዘርፍ በጀት ከ8-9 በመቶ በመሆኑ ከተቀመጠው መለኪያ አንጻር እሩቅ ያለነው። ከሌሎች ሀገራት ስለጤና የሆነ አካል እንዲያማክረን፣ ልምድ እንዲሰጠን አሊያም እንዲያስተምረን ከመጠበቅ ይልቅ በጤና ባለሙያዎቻችን ላይ መሥራት አለብን" ብለዋል።

ዶ/ር ደረጄ ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን አበረታች ውጤቶችም አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0