የናይጄሪያ አንጄሊካን ቤተ-ክርስቲያን በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ እና በሴት ሊቀ ጳጳስ ዙሪያ በተፈጠረ ክፍፍል ከእንግሊዝ ቤተ-ክርስቲያን መለየቷን አስታወቀች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየናይጄሪያ አንጄሊካን ቤተ-ክርስቲያን በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ እና በሴት ሊቀ ጳጳስ ዙሪያ በተፈጠረ ክፍፍል ከእንግሊዝ ቤተ-ክርስቲያን መለየቷን አስታወቀች
የናይጄሪያ አንጄሊካን ቤተ-ክርስቲያን በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ እና በሴት ሊቀ ጳጳስ ዙሪያ በተፈጠረ ክፍፍል ከእንግሊዝ ቤተ-ክርስቲያን መለየቷን አስታወቀች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.10.2025
ሰብስክራይብ

የናይጄሪያ አንጄሊካን ቤተ-ክርስቲያን በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ እና በሴት ሊቀ ጳጳስ ዙሪያ በተፈጠረ ክፍፍል ከእንግሊዝ ቤተ-ክርስቲያን መለየቷን አስታወቀች

ኤጲስ ቆጶስ ሳራ ሙላሊ የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ የናይጄሪያ ቤተ-ክርስቲያን በመሪዋ በታላቁ ካህን ሄንሪ ንዱኩባ በኩል መስከረም 23 የተሰማውን ውሳኔ “አስደንጋጭ” እና “ተቀባይነት የሌለው” ስትል አውግዛዋለች፡፡ ይህም የዓለም አቀፉን አንጄሊካን ቤተ-ክርስቲያን ፅኑ እምነት ችላ በማለት የተካሄደ ነው ስትል ገልፃለች።

የእንግሊዝ ቤተ-ክርስቲያን ለተመሳሳይ ጾታ ጥንዶች የሰጠችውን ፍቃድ፤ ሙላሊ “የተስፋ ወቅት” በማለት በ2023 የሰጡትን አስተያየት በማስታወስ፤ እንዲህ አይነት አቋም ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀውን የእንግሊዝ አብያተ ክርስትያናት ክፍፍል ያባብሳል ስትል የናይጄሪያ አንጄሊካን ቤተ-ክርስቲያን አስታውቃለች።

በተጨማሪም በእንግሊዝ እና በመላው ዓለም የሚገኙ ፅኑ የቤተ-ክርስትያኗ አባላት “አምላካዊ ያልሆኑ ትምህርቶችን” በመቃወም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት በፅናት እንዲያስቅጥሉ አሳስባለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0