የማሊ አማፂያን የኤፍፒቪ ድሮን አጠቃቀም ሥልጠና በዩክሬን እንደተሰጣቸው አመኑ
17:10 07.10.2025 (የተሻሻለ: 17:14 07.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የማሊ አማፂያን የኤፍፒቪ ድሮን አጠቃቀም ሥልጠና በዩክሬን እንደተሰጣቸው አመኑ
አማጺያኑ ወደ ማሊ ከተመለሱ በኋላ ያገኙትን ሥልጠና ለሌሎች ተዋጊዎች እንዳጋሩ የቡድኑን ቃል አቀባይ ጠቅሰው መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡
ማሊ ከዩክሬን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሐምሌ 29፣ 2016 አቋርጣለች፡፡ ውሳኔው የዩክሬን ባለሥልጣናት የማሊ ታጣቂዎች "አስፈላጊ መረጃ እና ተጨማሪ ነገሮችም" እንደተሰጣቸው መግለፃቸውን ተከትሎ የመጣ ነው፡፡
ሩሲያን በጦር ግንባር ማሸነፍ ያልቻለችው ኪዬቭ ለሞስኮ ወዳጅ በሆኑ የአፍሪካ ሀገራት የሽብር ቡድኖችን በማስታጠቅ በአፍሪካ ሁለተኛ ግንብር ለመክፈት ወስናለች ሲሉ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ ማሪያ ዛካሮቫ ቀደም ብለው ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
የዩክሬን አሠልጣኞች በሶሪያ ለሚገኙ ሽብርተኞች የካሚካዜ ድሮኖች አጠቃቀም ሥልጠና እንደሰጡ በ2024 የስፑትኒክ የምርመራ ዘገባ አጋልጧል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X