ዩክሬን ያለ ምዕራባውያን ይሁንታ በአፍሪካ ግጭቶች ላይ ተሳትፎ ልታደርግ አትችልም - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱዩክሬን ያለ ምዕራባውያን ይሁንታ በአፍሪካ ግጭቶች ላይ ተሳትፎ ልታደርግ አትችልም - ባለሙያ
ዩክሬን ያለ ምዕራባውያን ይሁንታ በአፍሪካ ግጭቶች ላይ ተሳትፎ ልታደርግ አትችልም - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.10.2025
ሰብስክራይብ

ዩክሬን ያለ ምዕራባውያን ይሁንታ በአፍሪካ ግጭቶች ላይ ተሳትፎ ልታደርግ አትችልም - ባለሙያ

“ዩክሬን በሱዳን የምታደረገው ማንኛውም ድርጊት በምዕራባውያን የተላለፈ ነው” ሲሉ በጆሃንስበርግ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ዶክትሬት ጥናት ባልደረባ ሲዞ ንካላ ለሱፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ዩክሬን በተለይም በአማፅያን ወገን ተሰልፋ በአፍሪካ ግጭቶች ውስጥ የምታደርገው ተሳትፎ ቅቡልነት ያለው መንግሥት ቁጥጥር፣ ሰላምና መረጋጋትን ለመመለስ የሚያደረገውን ጥረት የሚሸረሽር ነው ሲሉ ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡

እንደ ንካላ ገለፃ፤ እንደ ዩክሬን ያሉ የውጭ ኃይሎች ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማስጠበቅና የጦር መሳሪያዎቻቸውን ለማሟሸት ሆን ብለው ግጭቶቹ እንዲራዘሙ ያደርጋሉ፡፡

የዩክሬን ቅጥረኞች የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ አማፂያንን ወግነው በመፋለም ላይ መሆናቸውን አስመልክቶ የወጡት የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች፤ ዩክሬን ከአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ይሸረሽራል፡፡ ዩክሬን አማፂ ኃይሎችን በመደገፍ ሰብዓዊ ቀውሱን እንዳባባሰች፣ በአፍሪካ ኅብረት የሚመራውን የሰላም ጥረት እንዳሰተጓጎለች እና የአፍሪካን ጥቅም ችላ እንዳለች ተመራማሪው ተናግረዋል።

ዩክሬን በአፍሪካ ቅጥረኞችን በመደገፍ ተሳትፎ እንዳላት እየታወቀ ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ዝምታን መምረጣቸው፤ ለዩክሬን በሚደረገው ድጋፍ ዙሪያ ጫና በመቀነስ የምዕራባውያንን ፍላጎት የሚያገልገል ስልሆነ አያስገርምም ብለዋል፡፡

"የምዕራቡ ዓለም አጀንዳ እንደ ቻይና እና ሩሲያ ያሉ የጂኦፖለቲካዊ ተቀናቃኞቻቸው አፍሪካ ውስጥ ስማቸው እንዲጠለሽ ማድረግ ነው። ይህ ድርብ መስፈርት እንደሆነ ግልፅ ነው። በሱዳን የዩክሬን ተንኮሎች በተመሳሳይ ኃይል መወገዝ አለባቸው፡፡"

ተመራማሪው በሱዳን ያለውን ሁሉንም የውጭ ጣልቃገብነት አውግዘው፤ የአፍሪካ ሀገራት ዩክሬን ቅጥረኞቿን እንድታስወጣ ጫና እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡ በአፍሪካ የጋራ አቋም ከሌለ አህጉሪቱ የውጭ ኃይሎች በድንበሯ ውስጥ ግጭት እንዳይፈጥሩ ለመከላከል እንደሚቸግራት አስጠንቅቀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0