የኢትዮጵያ ባሕላዊ ምግቦች በባለኮኮብ ሆቴሎች የምግብ ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ ሊደረግ ነው
15:28 07.10.2025 (የተሻሻለ: 15:34 07.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ባሕላዊ ምግቦች በባለኮኮብ ሆቴሎች የምግብ ዝርዝር ውስጥ እንዲካተቱ ሊደረግ ነው
“በሀገራችን የሚገኙ ባሕላዊ ምግቦችና መጠጦች ከአካባቢው ማህበረሰብ አልፎ በሌሎች አካባቢዎች በትልልቅ ሆቴሎች የምግብ ዝርዝር ውስጥ እንዲገኙ እና እንዲተዋወቁ እየተሠራ ነው” ሲሉ የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታሰብ ስዩም ተናግረዋል፡፡
ለዚህም ይረዳ ዘንድ 205 የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ባሕላዊ ምግቦችን እንዲሁም ጠላ፣ ጠጅ እና አረቄን ሳይጨምር 15 ዓይነት ባሕላዊ የመጠጥ ዓይነቶች ላይ ኢንስቲትዩቱ ጥናት ማድረጉን ገልፀዋል፡፡
የዓለም ቱሪዝምን ቀን ምክንያት በማድረግ የተቋሙ ባለሙያዎች በባሌ ዞን የሚዘወተሩ ባሕላዊ ምግቦች ላይ ጥናት አድረገዋል፡፡ በባሌ ዞን አስተዳደር ከኢንስቲትዩቱ አሰልጣኞች ጋር የተሠናዳው የምግብ፣ የጉዞ ጥቅል እና የቱሪዝም ሀብቶች ካርታን የያዘ የጥናት ሰነድ ርክክብም ተደርጓል፡፡
⭐ መሰል የባሕላዊ የምግብ ሰነዶች ተዘጋጅተው በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ምግብ ዝርዝር ውስጥ እንዲቀርቡ መደረጉ ተጠቅሷል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X