የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋዛ ንግግር አሁናዊ ሁኔታ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል
14:46 07.10.2025 (የተሻሻለ: 16:14 07.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኳታር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋዛ ንግግር አሁናዊ ሁኔታ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል
በቃል አቀባዩ ማጀድ ቢን ሞሀመድ አል-አንሳሪ የተሰጡ ቁልፍ መግለጫዎች፦
🟠 በጋዛ ሰርጥ ጦርነት ዙሪያ 4 ሰዓታትን የፈጀ ድርድር ትናንት በሻርም አል-ሼክህ ተካሂዷል፡፡
🟠 ዛሬ በትራምፕ የሰላም እቅድ ዙሪያ የሚደረገው ሌላኛው ዙር ድርድር በሻርም አል-ሼክህ ይቀጥላል፡፡
🟠 በርካታ የትራምፕ እቅድ ዝርዝር ጉዳዮች አሁንም ስምምነት ይፈልጋሉ፡፡
🟠 የትራምፕ የጋዛ እቅድ ባይሳካ፤ ሌላ አማራጭ ላይ ለመነጋገር ግዜው በጣም ገና ነው፡፡
🟠 የትራምፕ የጋዛ እቅድ 20 ዋነኛ ነጥቦችንና በርካታ ዝርዝሮችን አካቷል፡፡
🟠 በትራምፕ እቅድ መሠረት የሃማስ ታጋቾችን መልቀቅ የጦርነቱ ማብቂያ ነው፡፡
🟠 ሁሉም ወገኖች በትራምፕ እቅድ ዙሪያ ተስማምተዋል፤ አሁን ተግዳሮቱ ትግበራው ላይ ነው፡፡
🟠 ኳታር በጋዛ ያለው ጦርነት እንዲያበቃ፣ የእስራኤልን ወረራ ለማስቆምና ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ቁርጠኛ ናት፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X