ዚምባብዌ ለአዳጊዎች ሀገር አቀፍ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ 1.9 ሚሊዮን ዶላር መደበች
14:03 07.10.2025 (የተሻሻለ: 16:14 07.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዚምባብዌ ለአዳጊዎች ሀገር አቀፍ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ 1.9 ሚሊዮን ዶላር መደበች
በጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዳግላስ ሞምበሾራ የተጀመረው ዘመቻ፤ ከ6-59 ወራት እድሜ የሆኑ ሁሉንም ህጻናት ያካትታል፡፡ በዚህም ነፃ የኩፍኝ ክትባት እና የቫይታሚን ኤ ማሟያ በየአካባቢው በሚገኙ ክሊኒኮች፣ ሆስፒታሎች እና የክትባት መስጫ ጣቢያዎች እንደሚቀርብ ተገልጿል።
በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ሚኒስትሩ ሞምበሾራ፤ ወላጆችና ሞግዚቶች ልጆቻቸውን በአቅራቢያቸው ወዳለ የክትባት ጣቢያ እንዲወስዱ በመጠየቅ፤ በግል እምነት ምክንያት በክትባት ዙሪያ የሚታየውን ማመንታት በቀጥታ በንግግራቸው አንስተዋል፡፡
በመንግሥት የሚመራው ዘመቻ በሐይማኖት፣ በባሕል እሳቤና በማህበራዊ ሁኔታ ሳይገድብ ለሁሉም ህፃናት የሚሰጥ በመሆኑ የትኛውም ታዳጊ በምንም ምክንያት ህይወት አድን የሆነው ክትባት ሊያልፈው አይገባም ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X