የሩሲያ ፓትሪያርክ በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየሩሲያ ፓትሪያርክ በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ
የሩሲያ ፓትሪያርክ በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.10.2025
ሰብስክራይብ

የሩሲያ ፓትሪያርክ በምንጃር ሸንኮራ አረርቲ ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ለግንባታ የተረበረበ እንጨት ተደርምሶ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

ፓትርያሪክ ኪሪል፤ በድንገተኛ አደጋው በርካታ ምዕመናን ለሞት እና ለአካል ጉዳት በመዳረጋቸው ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል ማለታቸውን በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

“እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠብቁት መልካም ነው፡፡ የአገልጋዮቹን ነፍስ ይማርልን፣ በቀኙ ያውላቸው፣ ለተጎዱትም ምህረቱን በቶሎ እንዲያደርግላቸው እና በክስተቱ ሀዘን ውስጥ ለገቡ ሁሉ ጥንካሬንና መፅናናትን እንዲያድላቸው እመኛለው” ሲሉ ፓትሪያርክ ኪሪል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

መስከረም 21፣ 2018 ዓ.ም በደረሰው አደጋ ቢያንስ 36 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0