ጥንታዊው ሀውልት ከግብፅ ኔክሮፖሊስ ሳቃራ የቅርስ ሥፍራ መጥፋቱ ተሰማ
11:22 07.10.2025 (የተሻሻለ: 11:54 07.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጥንታዊው ሀውልት ከግብፅ ኔክሮፖሊስ ሳቃራ የቅርስ ሥፍራ መጥፋቱ ተሰማ
ከስድስተኛው የግብፅ ስርወ መንግሥት ጀምሮ የ4 ሺ ዓመታት ዕድሜን ያስቆጠረው የኖራ ድንጋይ ሀውልት ከ2019 ጀምሮ ለሕዝብ እይታ ዝግ ከተደረገው የሳቃራ መቃብር ሥፍራ ተሰርቋል፡፡
የሀገሪቱ የቅርስ ሚኒስቴር ይህን ያሳወቀው በቅርቡ 3 ሺ ዓመታትን ያስቆጠረው የወርቅ አምባር ከካይሮ ሙዚዬማ መሰረቁ ከተነገረ በቅርብ ግዜ ውስጥ ነው፡፡ አምባሩ እንዲቀልጥ ተደርጎ በ3 ሺህ 400 ዶላር ብቻ እንዲሸጥ መደረጉ የተገለፀ ሲሆን የሙዚዬሙ አዳሽን ጨምሮ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
እነዚህ ክስተቶች ለጥቅምት 22 ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት አዲሱ ታላቁ የግብፅ ሙዚዬም ምርቃት አንድ ወር ሲቀረው መሰማታቸው ስጋትን ፈጥሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X