ደቡብ አፍሪካ የሀገሪቱን የንግድ አጋሮች ለማብዛት ያለመውን እቅድ ይፋ አደረገች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱደቡብ አፍሪካ የሀገሪቱን የንግድ አጋሮች ለማብዛት ያለመውን እቅድ ይፋ አደረገች
ደቡብ አፍሪካ የሀገሪቱን የንግድ አጋሮች ለማብዛት ያለመውን እቅድ ይፋ አደረገች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.10.2025
ሰብስክራይብ

ደቡብ አፍሪካ የሀገሪቱን የንግድ አጋሮች ለማብዛት ያለመውን እቅድ ይፋ አደረገች

"የደቡብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ፕሮግራም አካል የሆነው ዘጠነኛው እቅድ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ያለንን ተሳትፎ ማጠናከርና የቀረጥ እና ቀረጥ ነክ ያልሆኑ ተፅዕኖዎችን ለመቅረፍ የንግድ አጋሮቻችን ማብዛት ላይ ያነጣጠረ ነው" ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ የኢኮኖሚ ትግበራ እቅዱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ተናግረዋል፡፡

ይህ ውሳኔ በታሪፍ ወጀብ ተፅዕኖ የደረሰባችውን ዘርፎች ለመደገፍ የሚውል አስቸኳይ የኢንዱስትሪ ጥቅል ያካተት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

"በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስር ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን እናስፋፋለን ወደ ብሪክስ ሀገራትም እንዲሁ፤ በእርግጥም ወደ ሌሎች ገበያዎች የምናደረጋቸውን የገበያ ተደራሽነት በጊዜ ሂደት ተግባራዊ እናደርጋለን" ብለዋል ራማፎሳ።

አሜሪካ በደቡብ አፍሪካ ምርቶች ላይ ከነሃሴ 1 ጀመሮ የ30 በመቶ ቀረጥ ጥላለች። ከሀገሪቱ ጋር ሚዛናዊ የንግድ ግንኙነት እንዲኖር ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ራማፎሳ አረጋግጠዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት ምርቶች ወደ አሜሪካ እንዲገቡ የሚያስችለው የአፍሪካ ዕድገት እና ዕድል ድንጋጌ መስከረም 20 የአገልግሎት ጊዜው አብቅቷል።

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0