ማዳጋስካር አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱማዳጋስካር አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች
ማዳጋስካር አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.10.2025
ሰብስክራይብ

ማዳጋስካር አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሾመች

ከሳምንት በፊት መንግሥታቸውን የበተኑት ፕሬዝዳንት ራጆሊና፤ የቀድሞ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ወታደራዊ ካቢኔ ዳይሬክተር ጀነራል ሩፊን ፎርቱናት ዛፊሳምቦን በተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ክርስቲያን ንፃይን ቦታ ተክተዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ራጆሊና አዲሱን ሹመት ከመስጠታቸው አስቀድሞ ሀገሪቱ ስርዓትና የሕዝብ አመኔታን የሚመልስ ጠቅላይ ሚኒስትር ያስፈልጋታል ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዛፊሳምቦ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎትና የውሃ አቅርቦትን ወደነበረበት መመለስ ቀዳሚ ተግባራቸው እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

አንታናናሪቮን ማዕከል ያደረገውና በውሃና ኃይል አቅርቦት እጥረት ምክንያት የተነሳው ተቃውሞ በመስከረም ወር በማዳጋስካር መቀስቀሱ ይታወሳል፡፡

ፕሬዝዳንት ራጆሊና ካቢኔያውቸውን ቢያሰናብቱም የተቃውሞ ሰልፈኞች የሀገሪቱ መሪ ሥልጣናቸውን በፍቃዳቸው እንዲለቁ ሲገልፁ ቆይተዋል፡፡

በእንግሊዝኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0