በተያዘው በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ የማር ምርት ደረጃ ለመተግበር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል - የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበተያዘው በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ የማር ምርት ደረጃ ለመተግበር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል - የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት
በተያዘው በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ የማር ምርት ደረጃ ለመተግበር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል - የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 07.10.2025
ሰብስክራይብ

በተያዘው በጀት ዓመት ለኢትዮጵያ የማር ምርት ደረጃ ለመተግበር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል - የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና አባልነትና የዓለም ንግድ ድርጅትን የመቀላቀል ጉዞ በውጤታማነት ለመምራት የኢትዮጵያን ምርቶች ጥራት የማስጠበቅ ጉዳይ ትኩረት ይሻል ሲሉ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወንድማገኝ አሰፋ ተናግረዋል።

በዚህም የማር ምርትን ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ጋር በመተባበር የንብ ማነቢያ ቀፎ፣ የማር ምርት ማሸጊያና ማጓጓዣ ላይ አስገዳጅ ደረጃ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

የማር ምርታማነት ደረጃውም አስገዳጅ የአመራረት መስፈርቶችን በማካተት ጤንነቱና ደኅንነቱ የተጠበቀ ማር ለማምረት እና ዘመናዊ የማር አቆራረጥ ሥርዓትን መዘርጋት የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።

ዩኒዶ በበኩሉ የኢትዮጵያን ተስማሚነትና ምዘና የላቦራቶሪ አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ ድጋፎች እያደረገ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0