የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቬትናም የሚያደረገውን ሳምንታዊ በረራ ፍላጎትን ተገን አድርጎ ለመጨመር ማቀዱን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቬትናም የሚያደረገውን ሳምንታዊ በረራ ፍላጎትን ተገን አድርጎ ለመጨመር ማቀዱን አስታወቀ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቬትናም የሚያደረገውን ሳምንታዊ በረራ ፍላጎትን ተገን አድርጎ ለመጨመር ማቀዱን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 06.10.2025
ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቬትናም የሚያደረገውን ሳምንታዊ በረራ ፍላጎትን ተገን አድርጎ ለመጨመር ማቀዱን አስታወቀ

በሐምሌ ወር ወደ ሃኖይ መብረር የጀመረው ግዙፉ የአፍሪካ አየር መንገድ፤ አሁን ላይ በሳምንት አራት ግዜ ካርጎን ጨምሮ የቀጥታ በረራ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

“የእኛ ግብ የቬትናምን የዓለም አገናኘነት ሚና በማሳደግ ለሀገሪቱ ላኪዎችና ነጋዴዎች ታማኝ የካርጎ አገልግሎት መስጠት ነው" ያሉት በቬትናም የአየር መንገዱ ዋና ተወካይ ልዑልሰገድ ደሳለኝ፤ ፍላጎት ከጨመረ የበረራ ቁጥሩን ከፍ ለማድረግ ውጥን እንዳለ ጠቁመዋል።

ከ66 በላይ የአፍሪካ መዳረሻዎችና 145 ዓለም አቀፍ የበረራ መስመሮች ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ የቬትናም ተጓዥችን ከአፍሪካ፣ አውሮፓ እና አሜሪካ ጋር ያለምንም እንከን በማገናኘት ላይ እንደሚገኝ ቬትናም ኒውስ አስነብቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0