በአፍሪካ የመጀመሪያው ድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ልዑክ ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ጀመረ
21:32 06.10.2025 (የተሻሻለ: 21:44 06.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በአፍሪካ የመጀመሪያው ድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ልዑክ ከናይሮቢ ወደ አዲስ አበባ ጉዞ ጀመረ
በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት በኬንያ የኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ፤ ኢትዮጵያ የነዳጅ መኪኖችን አግዳ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማስተዋወቅ በንፁህ ኃይል ዘርፍ መሪነቷን ማጠናከሯን አንስተዋል፡፡
ጉዞው ኢትዮጵያ እና ኬንያ በድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ እንቅስቃሴ ከብሔራዊ ድንበሮቻቸው ባለፈ መተባበር እንደሚችሉ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
1 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ይህ ጉዞ በኪንያ ናይሮቢ ኡሁሩ ፓርክ መስከረም 25 በይፋ ተጀምሯል። ተሽከርካሪዎቹ ከአፍሪካ ኢ-ሞቢሊቲ ሳምንት አስቀድሞ መስከረም 30 አዲስ አበባ ይደርሳሉ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

