የአኅጉሪቱን የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ሥርዓት ለማሳደግ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ቁልፍ ጉዳይ ነው - የዘርፉ ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የአኅጉሪቱን የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ሥርዓት ለማሳደግ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ቁልፍ ጉዳይ ነው - የዘርፉ ባለሙያ

የአፍሪካ ሀገራት ለመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልገሎት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት አስፈላጊውን ግብዓት ማሟላት እንዳለባቸው የሜዲስን ፎር ሂዩማኒቲ የፕሮግራም ዳይሬክተር ኬኔት ኤን ሙኮ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ተዘንግቶ የቆየው ሀገር በቀል የሕክምና ዕውቀት ለአሕጉሪቱ የጤና ዘርፍ መሻሻል ትልቅ እገዛ እንዳለውም ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ አንስተዋል፡፡

"እንደ አለመታደል ሆኖ አፍሪካ ውስጥ በምዕራባውያን ሕክምና ላይ ከፍተኛ ጥገኝነት አለ። ይህን ሁኔታ ለመቀየር መንግሥታት ባሕላዊ ሕክምና ለዘርፉ ያለውን አበርክቶ በውል ተረድተው ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ አለባቸው" ብለዋል።

ትኩረቱን በመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ላይ ያደረገ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0