የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) ከፍተኛ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
19:45 06.10.2025 (የተሻሻለ: 19:54 06.10.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) ከፍተኛ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
በ2023/24 በጀት ዓመት 9.48 ሚሊዮን ዶላር ትርፍ ማግኘቱን ሪፖርት አድርጓል፡፡
ለትርፉ ምክንያት ያላቸው፦
🟠 የንግድ ገቢ መጨመር፣
🟠 አዳዲስ ስፖንሰሮች፣
🟠 ጠንካራ የፋይናንስ ቁጥጥር ስርዓት ተግባራዊ ማድረጉ፡፡
ካፍ ያሳወቀው አጠቃላይ ገቢ 166.42 ሚሊዮን ዶላር እንደሚደርስ የተገለፀ ሲሆን ተቋሙ ወጪዎቹን በዘርፍ አከፋፍሏል፦
🟠 81 ሚሊዮን ዶላር ለውድድር ሽልማት፣
🟠 19 ሚሊዮን ዶላር ውድድሮችን ለማዘጋጀት፣
🟠 35 ሚሊዮን ዶላር ለእግር ኳስ ልማት፣
🟠 21 ሚሊዮን ዶላር ለአመራርና ለአስተዳደር ዘርፍ፡፡
የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትስፔ፤ አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የረዥም ግዜ የገበያና የቴሌቪዥን ስምምነት ለመፈፀም መቃረባቸውንም አስታውቀዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X