ኢትዮጵያ የጤና ኤክስቴንሽን ልምዷን ለአፍሪካ ሀገራት ማካፈል አለባት - የሲዳማ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የጤና ኤክስቴንሽን ልምዷን ለአፍሪካ ሀገራት ማካፈል አለባት - የሲዳማ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊ

ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ፤ የአፍሪካ ሀገራት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ የሚያደርግ የጤና አገልግሎት የመፍጠርን አብነት ከኢትዮጵያ ሊወስዱ እንደሚገባ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ኃላፊው የአሕጉሪቱን የጤና ዘርፍ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍ ጥገኝነት ማላቀቅ እንደሚገባም አጽዕኖት ሰጥተዋል።

"በአሁኑ ጊዜ በጤናው ዘርፍ ላይ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍ እያሽቆለቆለ ይገኛል። በዚህም ክፍተቶችን በዘላቂነት ለመሙላት የሀገር ውስጥ ፋይናንስን ማሳደግ አማራጭ የሌለው ነው" ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0